


ኩዊር ኢትዮጵያ
ኩዊር ኢትዮጵያ የተለያዩ ስርዓተ ፆታዊና ወሲባዊ ማንነት ላላቸው ኢትዮጵያዊ ኩዊር ሴቶች እንዲሆን ታስቦ በኩዊር ሴቶች የተመሠረተ አማራጭ ምኅዳር ነው። ይኽውም ሌዝቢያን፣ ባይሴክሽዋል ወይም ኤሴክሽዋል የሆኑ ሴቶችንንና ትራንስ ሴቶችን ያካትታል። ይህ ምኅዳር የኩዊር ማኅበረሰብ ታሪክ እና የሕይወት ልምድ ትልቅ ሥፍራ የሚይዝበት ነው። እንደ’ኩዊር ማኅበረሰብ የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን ገጠመኞች፤ የተለያዩ ሰዎችን የግል ታሪኮች፤ ቃለ- መጠይቆች እንዲሁም ሥነ-ጥበባትን እንደምናካትት ተስፋ እናደርጋለን። ከነዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ እና በዳያስፖራ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ራሳቸውን ሆነው የሚመጡበት የበይነ-መረብ ማኅበረሰብ መድረክ ሆኖ እንዲያገለግል ማስቻል ፍላጎታችን ብቻ ሣይሆን ጥረታችንም ጭምር ነው። በ etqueerfamily@gmail.com ልትጽፉልን ትችላላችሁ።